የመፅሐፍ ምረቃ

የመፅሐፍ ምረቃ

የልማት አርበኛው የማሩ አበበ የህይወት ታሪክ በመጽሀፍ ወጣ

 በጋዜጠኞቹ ዓይናለም ሀድራ እና እዝራ እጅጉ የተዘጋጀው የአቶ ማሩ አበበን የህይወት ታሪክ የሚዳስሰው መጽሀፍ እሁድ ግንቦት 20 2015 ዓ.ም 5 ኪሎ በሚገኘው በቅርስ ባለስልጣን አዳራሽ ከጠዋቱ 4 ሰአት ጀምሮ ይመረቃል፡፡
አቶ ማሩ አበበ ከ7 ዓመት አስቀድሞ በወርሀ ሰኔ ህይወታቸው ያለፈ የሀገር ባለውለታ ነበሩ፡፡
የአቶ ማሩ አበበ ቤተሰቦች ከተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን ጋር በጋራ ያዘጋጁት ይህ መሰናዶ ባለታሪኩ ህይወታቸው ያለፈበትንም 7ኛ አመት በልዩ ልዩ መሰናዶዎች ያስባል፡፡
ታሪካቸው በመጽሀፍ የተሰነደላቸው የደን ልማት ባለሙያው አቶ ማሩ ኮተቤ ኪዳነምህረትን እንዲሁም አሁን እንጦጦ ፓርክ የተሰራበትን ስፍራ በማልማት ለሀገር ጠቃሚ ተግባር ያከናወኑ ናቸው፡፡ ከደን ልማቱም ባሻገር በመንገድ ቅየሳ የጎላ ሚና አበርክተዋል፡፡ አቶ ማሩ አበበ ለሀገር ትልቅ ስራ በማበርከታቸው መታሰቢያ ይሆን ዘንድም በስማቸው በደቡብ ወሎ ዞን ት/ቤት ተሰይሞላቸዋል፡፡
አቶ ማሩ አበበ ከወጣትነታቸው ጊዜ አንስቶ በደን ልማት፣ ችግኝ በመትከል አካባቢን በመጠበቅ ለሀገር የሚጠቅም ጉልህ ተግባር አከናውነዋል፡፡
የ7ኛ ዓመት የማስታወሻ መሰናዶው በልዩ ልዩ ዝግጅቶች የሚታሰብ ሲሆን በእርሳቸው ህይወት ላይ ያተኮረ አጭር ፤ በሽለላ እና በፉከራ የታጀበ ድራማ ይቀርባል፡፡
በተጨማሪም ከመጽሀፉ የተወሰኑ ገጾች የሚነበቡ ሲሆን የአቶ ማሩ የቅርብ ሰዎችም ስለ አቶ ማሩ ምስክርነታቸውን ይሰጣሉ ተብሏል፡፡
የግብርና ባለሙያዎች ፤ ከፍተኛ የመንግስት ሰዎች ፤ ከደን ልማት ጋር በተያያዘ የሚሰሩ ግለሰቦችና ተቋማት በማስታወሻ መርሀ-ግብሩ ላይ በተጋባዥነት የሚታደሙ ሲሆን የህይወት ታሪካቸው ላይ ያተኮረው መጽሀፍም በይፋ ይመረቃል ፡፡

Signin & Rate
Leave a Comment

Event Details